Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

mpdc

MPDC

በከለላ ትእዛዞች የራስዎን ደህንነት መጠበቅ

በከለላ ትእዛዞች የራስዎን ደህንነት መጠበቅ

የከለላ ትእዛዝ ማግኘት

በሚያስከትል ግንኙነት ውስጥ ሲሆኑ ወይም ከዚያ በኋላ የራስዎን ደህንነት ለመጠበቅ ብዙ እርምጃዎች አሉ። እርስዎ የሲቪል የከለላ ትእዛዝ (Civil Protection Order, CPO) ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ። ዳኛው በጥያቄዎ ከተስማማ፣ ጊዜያዊ የከለላ ትእዛዝ (Temporary Protection Order, TPO) ወዲያውኑ ይሰጣል። ጊዜያዊ የከለላ ትእዛዝ የሚጸናው ለ14 ቀናት ነው እና የሚሰጠው አድራሹ በሲቪል የከለላ ትእዛዝ ችሎት ለመቅረብ መጥሪያ እስኪደርሰው ድረስ ጊዜ ለመስጠት ነው። በድንገተኛ ሁኔታዎች እና ከመደበኛ የፍርድ ቤት የስራ ሰዓቶች ውጪ የድንገተኛ ጊዜ ጊዜያዊ የከለላ ትእዛዝ (Emergency Temporary Protection Order, ETPO) ሊሰጥ ይችላል። ይህ ትእዛዝ ለ 5 ቀናቶች የሚቆይ ነው እና መጀመር የሚችለው በፖሊስ ባለሟል እና ከተጎጂዎች እና የማብቃት ተከራካሪዎች (Survivors and Advocates for Empowerment, SAFE) ባለ ተከራካሪ መካከል የሚጀመር ነው።

የሲቪል ከለላ ትእዛዝ ምንድን ነው?

የሲቪል ከለላ ትእዛዝ ፣ ከጥቃት አድራሹ የረጅም ጊዜ ከለላ ለመስጠት የታቀደ ለአንድ አመት የሚቆይ በዳኛ የሚሰጥ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ነው። የሲቪል ከለላ ትእዛዝ ጥቃት አድራሹን ጥቃቱን እና/ወይም መዛቱን እንዲያቆም፣ ከእርስዎ እንዲርቅ፣ በማናቸውም መንገድ እርስዎን እንዳያገኝ፣ እና ደህንነት እንዲሰማዎ የሚያስችል ማንኛውም አይነት ሌሎች አይነት መፍትሄዎችን የሚሰጥ ነው።

ማን ማግኘት ይችላል?

እርስዎ የስጋ፣ የጉዲፈቻ፣ የጋብቻ ግንኙነት ካሎት፣ የኑሮ አጋር፣ ወይም በጋራ ልጅ ካሎት፣ ተመሳሳይ ቤት ከሚጋሩት ወይም ተጋርተውት ከሚያውቁት፣ የመተያየት ግንኙነት ካሎት ወይም አስቀድሞ ከነበሮት ሰው(ጾታዊ ግንኙነት መሆን አይጠበቅበትም) ወይም አሁን ካሎት የቤት ውስጥ አጋር ጋር ከላይ ያሉት አይነቶች ግንኙነቶች ከነበራቸው ሰው የአካል ጥቃት ከደረሰቦት፣ የወሲብ ጥቃት ከደረሰብዎት፣ ዛቻ፣ እና ያልተፈለገ ክትትል፣ ወይም ንብረትዎ ወድሞ ከሆነ የሲቪል ከለላ ትእዛዝ ማግኘት ይችላሉ። እርስዎ ከDC ፍርድ ቤት ከለላ ለማግኘት እርስዎ DC ውስጥ መኖር ወይም መስራት አለብዎ እና ቢያንስ አንዱ ክስተት በ DC ውስጥ የተፈጠረ መሆን አለበት። ነገር ግን፣ ትእዛዙ እርስዎን በሁሉም ክልሎች ይጠብቅዎታል።

ለሲቪል የከለላ ትእዛዝ መቼ ማመልከት አለብኝ?

ጥቃቱ ከተከሰተ በኋላ ወዲያውኑ፣ ወደ የቤት ውስጥ ጥቃት መቀበያ ማእከል ይሂዱ በ DC Superior Court, Room 4235, 500 Indiana Avenue, NW, Washington, DC ወይም በ United Medical Center at 1328 Southern Avenue, SE, Suite 311 ውስጥ በሚገኘው የሳተላይት የቤት ውስጥ ጥቃት መቀበያ ማእከል ይሂዱ። እርስዎ ከክስተቱ በኋላ እስከ ሁለት አመት ድረስ ፋይሉን ማቅረብ ይችላሉ፣ ነገር ግን ፋይሉን ለማቅረብ መዘግየት ዳኞች እርስዎን የሚያምኑበትን እድል እንዲያንስ ሊያደርግ ይችላል። የሲቪል ከለላ ትእዛዝ ፋይል የማቅረብ ሂደት ብዙ ሰዓታትን ሊወስድ ይችላል፣ ስለዚህ ከሰዓት ፍርድ ቤቱ ከሚዘጋበት ከሰዓት 4 ሰዓት በፊት በቂ ጊዜ እንዲኖርዎት በሚያስችልዎ መልኩ ቀደም ብለው መድረስዎን ያረጋግጡ።

ያስታውሱ፣ የሲቪል ከለላ ትእዛዝ ጥቃቱን ላያስቆም ይችላል። እንዲያም ቢሆን፣ ያጋጣምዎትን ልምድ በህግ እንዲመዘገብ የሚወስዱት አስፈላጊ እርምጃ ነው። እርስዎ የሲቪል ከለላ ትእዛዝ ካገኙ፣ የእርስዎን ደህንነት ለማቀድ ሊወስዷቸው ስለሚገቡ ሌሎች እርምጃዎች ያስቡ። የሚቀጥለው ክፍል ማድረግ የሚገባዎን ሀሳቦች ይሰጥዎታል።

ለተጨማሪ የቤት ውስጥ ጥቃት መረጃ፣

የቤት ውስጥ ጥቃት ክፍል (Domestic Violence Unit)
የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት (Police Headquarters)
300 Indiana Avenue, NW, Room 3156
Washington, DC
ስልክ፣ (202) 727-7137
ፋክስ፣ (202) 727-6491